Music Details

አንዳንድ ሰው አለ
ሴት የመሆን ዋጋ ልኬቱን እርቆ
ማንነቱን ቢያጣ በባዶነት ልቆ
የድንቁርና ጥግ ጓዙን ያሸከመው
ሚስቱ መናፈሻ መዝናኛ 'ምትመስለው
አንዳንድ ሰው አለ
የክፋትን በትር በፍቅር የሰበረ
ቅንነት የገዛው ለነፍሱ ያደረ
ንግግሩ ጥዑም የአንደበቱ ለዛ
ተሸናፊ ልቡ ልብን የሚገዛ
አንድ አንድ ሰው አለ
እራሱን የደለለ
በውሸት አለም ውስጥ ተደብቆ ያለ
በሰባራ ሚዛን ፍትህ እየመዘነ
አንዱ በበደለው ሺህ ሰው እየቀጣ
በጭካኔ ገዳም አለ እንደመነነ
አንዳንድ ሰው አለ
ከሰው ሰልፍ መሃል እያለ የሌለ
ከቁጥር መደዳ ከአንድ የጎደለ
በባዶነት ማሳ ቀድሞ የበቀለ
ከሰው ጋር የሚኖር አንቱ እየተባለ
አንድ አንድ ሰው አለ
ሲለግም ባይጣፍጥ : ድንጋይ ነው ተብሎ
መሬት የተጣለ
ልክ እንደ ገለባ መታየት ሲያበዛ
ንፍስ የበተነው ከአፈር እንደዋዛ
ውድ የመሆን ወርቁ ዝቅታ መሆኑ
ሳይገባው ያረጀ ያለቀ ዘመኑ
አንድ አንድ ሰው አለ
አንድ አንድ ሰው አለ
እያደር የሚያንስ ከርሞ የቀለለ
ከምስኪኑ ሰርቆ ሀብት እየቆለለ
ነፍሱን በወረቀት ብጣሽ የተመነ
አንድ አንድ ሰው አለ
አንድ አንድ ሰው አለ
ምላሽ የማይሻ : መስጠት የታደለ
ከውለታ ልቆ : ውለታው ያየለ
ከደግነት አምባ : ከጥንካሬ ጎን
እማ ስምሽ አለ
አንድ አንድ ሰው አለ
ክብርና ማዕረግ አይኑን የጋረደው
ያለእኔ ማነው ባይ ጉራ ያሳበደው
ስገዱልኝይላል : አንቱ በሉኝ ይላል ዙፋንላይእንዳለ..
ምድር እና ሰማይን የዘረጋውእንኳን: አንተ እየተባለ